ዜና | Oduu | News
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመራሮች ጋር በመሆን፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን የአራት ዓመታት ጉዞ የሚያሳይ ኤግዚቢሽን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመራሮች ጋር በመሆን፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን የአራት ዓመታት ጉዞ የሚያሳይ ኤግዚቢሽን ጎብኝተዋል። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !!

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና የሚድያ ቤተሰብ "ተስፋን እንተከል " በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ አኖሩ!

በቢሮው አስተባባሪነት እና አሰባሳቢነት፥ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አመራሮች፣ የመንግስት እና የግል ሚድያ አመራሮች፣ ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የኮሙኒኬሽን መዋቅር የኪነጥበቡ ቤተሰብ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የስፖርት ቤተሰብ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የማህበረሰብ አንቂዎች በጋራ በመሆን በዛሬው ዕለት የችግኝ ተከላ አካሔዱ። በመርሐ-ግብሩ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚኣብሄር በአስተላለፉት መልዕክት፣ “የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ተቋማት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ከተማ ባሉ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች የጀርባ አጥንት በመሆን በመንግስትና በህዝብ መካከል ድልድይ ሆኖ ከማገልገል በተጨማሪ፣ አሰባሳቢ የወል ትርክትን በማስረፅ፣ የሀገር አንድነት እና ሉአላዊነትን የጠራ ዕሳቤ ያለው ትውልድ ከመፍጠር አንፃር ትርጉም ያለው ስራ እየሰራ ይገኛል። እንዲሁም፥ የአረንጓዴ አሻራችን ሽፋን እና ስፋት ተከታታይ ዘገባዎችን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶችንና የዜና ሽፋኖችን በግንባር ቀደምነት የመረጃ ምንጭ ሆኖ በመስራት፣ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ፣ ጠንካራ ተግባቦት ከመፍጠር አንፃር ውጤታማ ስራ እየሰራ ይገኛል። ዛሬም የሚድያ ቤተሰብ ቀደም ሲል ከተጠቀሱት ቁልፍ ተግባራቱ በተጨማሪ፣ “ተስፋን እንትከል“ በሚል መሪ ቃል እንደ ሀገር 8 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል የተጀመረዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አንዱ አካል በመሆን የከተማዋን የአረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግ፣ የተፈጥሮ ሚዛን ለመጠበቅ፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት እና ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ ለመፍጠር በየካ ክፍለ ከተማ ቀበና የወንዝ ዳርቻ ተገኝተዉ ችግኝ በመትከል ታሪካዊ አሻራቸዉን ማኖራቸዉ፣ በአረንጓዴ አሻራ በዓለም መድረክ ያገኘነዉን እዉቅና ከማጠናከር ባሻገር ድርብ ኃላፊነታቸዉን መወጣት መቻላቸዉን ተግባራዊ ማሳያ ነው ሲሉ የቢሮዉ ኃላፊ ገልፀዋል። በመጨረሻም የሚድያው ቤተሰብ በከተማዋ ሁለንተናዊ አጀንዳዎች ላይ ግንባር ቀደም ሆነው በትዉልድ እና በሃገር ግንባታ ላይ ሙያዊ ግዴታቸዉን ለመወጣት ድርብ ኃላፊነት ያለባቸዉ መሆኑንና ይህንንም ወደ ተግባር ለዉጦ የተፈለገዉን ዉጤት ለማምጣት የጀመሩትን አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡ ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !!

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የደብረ ብርሃን ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያው ከልደታ ክፍለ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ።

የደብረ ብርሃን ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ የከተማዋን ፈጣን የኢንዱስትሪ እና የኢንቨስትመንት ዕድገት ሊመጥን የሚችል ጠንካራና ዘመናዊ የተግባቦት ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ የልምድ ልውውጥ ከአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ጋር አካሂዷል። ​በዕለቱ የልደታ ክፍለ ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሲፈን ባዩ እና የተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተቋማቸውን ግንባር ቀደም እና ተሸላሚ ያደረጉ ዘመናዊ አሠራሮችን ለደብረ ብርሃን ከተማ የኮሙኒኬሽን ልዑካን ቡድን በዝርዝር አቅርበዋል። ​በዋናነት በልምድ ልውውጡ የተቀሰሙ ምርጥ ተሞክሮዎች፦ በ​ዲጂታል ኮሙኒኬሽን የዲጂታል ሚዲያ አማራጮችን ለሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም፤​ የመረጃ አያያዝ ሥርዓትን፤ ዘመናዊና የተቀናጀ የኮሙኒኬሽን መረጃዎችን የማደራጀትና የመተንተን ብቃት፤ ​ሕዝባዊ ተሳትፎና ምላሽ ሰጪነት፤ የኅብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በማዳመጥና በኮሙኒኬሽን አግባብ አፋጣኝ ምላሽ የመስጠት ልምድ እና ​አካታችነት (Inclusivity) ማለትም ልዩ ትኩረት የሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ድምፅ የሚያስተጋቡ የሚዲያ ሥራዎችን ማከናወን የሚሉት ናቸው። ​የተቀሰሙ ምርጥ ተሞክሮዎች ወደ ተግባር እንደሚለወጡ የደብረ ብርሃን ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ይገርማል አበበ በመድረኩ አብራርተዋል። የደብረ ብርሃን ከተማ ግዙፍ የኢንዱስትሪ እምቅ አቅምና መልካም ገጽታ በአግባቡ ለመገንባት ተቋማዊ የኮሙኒኬሽን አቅምን ማሳደግ ወቅታዊና ጊዜው የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። ​ ከአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የተገኘው የተቀናጀ የተግባቦትና የቅንጅታዊ አሠራር ተሞክሮ በቀጣዩ የበጀት ዓመት ዕቅድ ውስጥ ተካቶ ወደ ተግባር እንደሚለወጥም ኃላፊው አረጋግጠዋል። ​የደብረ ብርሃን ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ ያካበቱትን ውጤታማ ተሞክሮ ያለስስት ላካፈሉ እና የላቀ አቀባበል ላደረጉላቸው የልደታ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። መረጃው የደብረብርሃን ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ የአገልግሎት አሰጣጡ ፈጣን እና ችግር ፈች እየሆነ ነው ሲሉ ተገልጋዮች ገለፁ

በአስተዳደሩ በተቀናጀ የአንድ ማዕከል እና በተቋማት የሚሰጠው አገልግሎት ውጤታማ መሆኑንም ተገልጋዮች ገልፀዋል። በአስተዳደሩ አገልግሎት ፈልገው የመጡ ነዋሪዎች እንደተናገሩት በልደታ ክ/ከተማ እየተሰጠ ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን፣ ምልልስን የቀነሰ እና ችግር ፈች እየሆነ ነው ብለው ይህ አሰራር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል በማለት ገልፀዋል። የአገልግሎት አሰጣጡ ተደራሸና የህብረተሰቡን ፍላጎት ያማከለ እየሆነ በመምጣቱ እጅግ ደስተኞች ነን ብለዋል ተገልጋዮች።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የሚኒ ሚዲያ ክበባት ዋና አላማ ተማሪዎች በስነ-ምግባር የታነፁ ሀገር ወዳድ ዜጋ እንዲሆኑ መስራት መሆኑ ተገለፀ፡፡

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች እየተሳተፉ ላሉ የሚኒ ሚዲያ ክበብ አባላት እና አማተር ጋዜጠኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሲፈን ባዩ በስልጠና ላይ እንዳሉት ትምህርት ቤቶች የሚኒ ሚዲያ አማራጮችን መዘርጋታቸው ተማሪዎች እውቀት፣ ክህሎትና ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። አያይዘው እንደ ተቋም በሀገር ደረጃ ትልቅ ስራ የሚሰሩ ታዳጊዎችን ለማፍራት ጽ/ቤቱ ሙያዊ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አንስተው የሚኒ ሚዲያ ክበባት ዋና አላማ ተማሪዎች በስነ-ምግባር የታነፁ ሀገር ወዳድ ዜጋ እንዲሆኑ መስራት መሆኑን ገልፀዋል። ተማሪዎች ዝንባሌያቸውን እንዲለዩ በማድረግ ስኬታማ ስራዎችን አብረን እንስራ ያሉት ወ/ሮ ሲፈን ሚኒ ሚዲያዎች ለተለያዩ ሙያዎች ትልቅ ግብዓት ናቸውና ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጧቸው ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡ በጽ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ባለሞያ የሆኑት አቶ አስቻለው ይርሰማ ስልጠናውን ሲሰጡ የሚኒ ሚዲያ ምንነት፣ አደረጃጀት፣ መረጃ አቀራረብ፣ ይዘት ቀረጻ እና ከአጠቃቀም አንጻር ሊያስከትል የሚችለውን አዎንታዊና አሉታዊ ተጽእኖ የተመለከቱ ነጥቦችን አብራርተዋል፡፡ የሚኒ ሚዲያ ክበባት ዋና አላማ በማዝናናት ማስተማር ነው ብለው ተማሪዎች ሀገር ተረካቢ እንደመሆናቸው ሚኒ ሚዲያው፤ ለተማሪዎች በሚመጥናቸው ቋንቋና የአቀራረብ ይዘት ተዘጋጅቶ ሊቀርብላቸው ይገባል ብለዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የአዲስ አበባ አስተዳደር ኮሚንኬሽን ቢሮ ባደረገው የ2017 ምዘና ከ11 ዱም ክ/ከተማ 1 ኛ ደረጃን በመያዝ ተሸላሚ ሆኗል።

ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ስትሰሩ ለነበራቹህ የክ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ፣ ለክ/ከተማ ጽ/ቤቶች፣ ለወረዳ ኮሙኒኬሽን መዋቅር፣ ለምክር ቤት ዘርፍ ኮሚቴ፣ ለማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች፣ለጽ/ቤቱ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ምስጋና እናቀርባለን። ድጋፋቹህ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ እንላለን። ወ/ሮ ሲፈን ባዩ :- የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የቂርቆስ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ከልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ።

የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሲፈን ባዩ በልምድ ልውውጡ ወቅት እንደተናገሩት የአሰራር ተሞክሮን መቅሰም ውጤታማ አገልግሎትን ለመስጠት ያስችላል ብለው ቂርቆስ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በክ/ከተማችን ተገኝቶ ላደረገው የልምድ ልውውጥም ምስጋና አቅርበዋል። የአሰራር ተሞክሮዎችን መለዋወጥ ስራዎችን በእውቀት ለመስራት ያስችላል ያሉት ኃላፊዋ እኛም ከእናንተ እናንተም ከእኛ የቀሰምናቸውን መልካም አሰራሮች በሙሉ አቅም ወደ ስራ በማስገባት የማህበረሰቡን የመረጃ ፍላጎት ማሟላት ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል። የቂርቆስ ክ/ከተማ አመራርና ባለሙያዎች በበኩላቸው የቀሰምነውን መልካም አሰራር ወደ ተቋማትን ወስደን በማስፋት ውጤታማ ስራ እንሰራለን ብለዋል።

image
image
image
image