image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋይና ባለድርሻ አካላት ሚና በተመለከተ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።

ሀምሌ 10, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ተገልጋዩ ለመገልገል ሲመጣ የሚጠበቅበትን ነገር በማሟላት የሚፈልገውን አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል ገልፀው አገልግሎቱ ቀልጣፋ እንዲሆን ያጎደልነውን ነገር ደግሞ በመወያየትና በመሙላት ቀልጣፍና ውጤታማ እንዲሁም አዳጊ የሆነ አገልግሎት መስጠት ተችሏል በማለት ገልፀዋል። በምንሰጠው አገልግሎት ማህበረሰባችንን ስናገለግል ነበር በማለት በሚሰጡ አገልግሎቶች ተገልጋዩ የሚያነሳቸውን ችግሮች እቅድ በማቀድ በአጭርና በረጅም ጊዜ ለመፍታት የቻልንበት አግባብ አለ ሲሉ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ገልፀዋል። ለህብረተሰብ እንቅፍት የሆነ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግር መንግስት ልዩ ትኩረት በመስጠት ስራዎችን መስራት ችሏል። በሚሰጡ አገልግሎቶች የመብራትና የሲስተም መቆራረጥ የሚመለከተው አካል ሀላፊነት ወስዶ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በቀጣይ ያሉትን ችግሮች ቀርፎ ለነዋሪዎቻችን ቀልጣፍ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል እየተሰራ ነው ብለዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሓፍቱ ብርሃኑ እንደገለፁት አገልግሎት ፈልጎ ከሚመጣው የማህበረሰብ ክፍል ጋር በመነጋገር ያሉትን ጥንካሬዎች በማስቀጠል ክፍተቶች ደግሞ በቀጣይ ቀርፎ ቀልጣፍ አገልግሎት መስጠት ይገባል ብለዋል። መንግስት ዘመኑን ተገልጋዩን በሚመጥን አግባብ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎቶችን እየሰጠ ነው ያሉት አቶ ሓፍቱ አያይዘው ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ለተገልጋዩ ግልፅ በማድረግ ፈጣን አገልግሎት መስጠት ላይ እየመጣ ያለውን ወጤት አጠናክሮ ማስቀጠል የተገልጋዩም የአገልጋዩም ሀላፊነት ነው በማለት ገልፀዋል። በአግባቡ አገልግሎት መስጠት ለህዝብ ዝቅ ብሎ ማገልገል ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሓፍቱ ብርሃኑ ከመንግስት ተቋም የሚሰጠው አገልግሎት ለትርፍ ሳይሆን እናንተ በምትከፍሉት ግብር ተቀንሶ የሚከፈለው ስለሆነ ማገልገል ግዴታው ነው ሲሉ ተናግረዋል። አገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ እንዲሆን እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል በማለት በቀጣይም ፈጣንና ቀልጠፋ አገልግሎ አሰጣጥ እንዲኖር እንደዚ አይነት የህዝብ መድረክ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች