image
image
image
image
image

"በአዲስ እይታ የልደታ ከፍታ" የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የአሰራር ልምዱን አካፈለ

ጥቅምት 16, 2018
የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሲፈን ባዩ በተሞክሮ ልውውጡ ወቅት ባስተላለፍት መልዕክት እንደተናገሩት የኮሙኒኬሽን መዋቅሩ ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖረው በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው የተሞክሮ ልውውጡም ይህንን ለማጠናከር ያስችላል ሲሉ ገልፀዋል። ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በተሰጠን አቅጣጫ መሰረት እርስ በእርስ መማማርን አዳብረን ጠንካራ የኮሙኒኬሽን ስርዓት እንዘረጋለን ብለዋል ወ/ሮ ሲፈን። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አብዱረዛቅ በበኩላቸው ያገኘነውን ልምድ በክ/ከተማችን በማስፋት ጠንካራ የኮሙኒኬሽን ስርዓት ለመገንባት የሚደረገውን ጉዞ ለማሳለጥ ሚናችንን እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች