image
image
image
image
image

"በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ' በሚል መርህ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ለማሳካት የሚታየው የአመራሩ ቁርጠኝነትና የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል" - ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ

ታህሳስ 7, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ" በሚል መርህ እየተከናወኑ የሚገኙ የአንድ ወር አፈፃፀም ከአጠቃላይ አመራሩ ጋር በመገምገም በቀጣይ ትኩረት በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ መድረኩን የመሩ ሲሆኑ በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ በሚል መርህ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ለማሳካት የሚታየው የአመራሩ ቁርጠኝነትና የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል። ኢንጂነር ወንድሙ አክለውም ተግባሩ ክፍለ ከተማውን አንድ እርምጃ ከፍ የሚያደርግ በመሆኑ ያለ ምንም መንጠባጠብ በውጤት ለማጠናቀቅ አመራሩ በ24/7 መርህ መስራት እንደሚገባው አፅንኦት ሰጥተዋል። የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በበኩላቸው በየደረጃው የመደመር መንግሥት የዘርፎች እመርታን ለማሳደግ የተሰጡ ሥልጠናዎችን መነሻ በማድረግ የነዋሪውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ዕቅድ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀዋል። በአንድ ወር የታየው አፈፃፀም አበረታች መሆኑን በማንሳት ተግባራቱን ከመደበኛ ዕቅዶች ጋር አጣጥሞ መምራት እንደሚገባ ወ/ሮ ልዕልቲ አሳስበዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍታለው ከፍያለው በመድረኩ እንዳሉት የተያዙት ዕቅዶች ልዩ ርብርብ የሚፈልጉ በመሆናቸው በውጤት ለማጠናቀቅ ሁሉም አካል በቁርጠኝነት ሊረባረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመድረኩ በአንድ ወር የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም የቀረበ ሲሆን የኑሮ ውድነትን ከመቀነስ አኳያ በተለይም የምርት አቅርቦትን ከማሳደግ እና ህገ ወጥነትን ከመከላከል፣ የሌማት ትሩፋት፣ ሌብነትን እና ብልሹ አሰራርን ከመቀነስ፣ ተረጂነትን ከመቀነስ፣ ከሰው ተኮር ተግባራት፣ ከገቢ አሰባሰብ እና ከአገልግሎት አሰጣጥ ስራ አኳያ የተሰሩ ተግባራት አፈፃፀም የተሻለ መሆኑ ተገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች