image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ 6 ወራት አፈፃፀም እውቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር አካሄደ።

የካቲት 14, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት የወረዳዎች አፈፃፀምና የበጎ ማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች እውቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር አካሂዷል። በእውቅና መድረኩ ላይ የልደታ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሲፈን ባዩ እንደተናገሩት ባለፉት ስድስት ወራት በህዝብና በመንግስት መካከል ድልድይ ሆኖ በማገልገል ለህብረተሰቡ ወቅታዊ፣ ፈጣን እና ጥራት ያላቸውን መረጃዎች በማድረስ ረገድ ስኬታማ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ስራዎች ማከናወኑን አንስተዋል። ወ/ሮ ሲፈን አክለው እንደገለጹት ተቋሙ በሀገራዊ እና ከተማዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጠር እንዲሁም ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ትኩረት አድርጎ መስራቱን ተናግዋል። ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የተለያዩ ጥናቶችን ከማካሄድ ባለፈ የሥራ ኃላፊዎች ከነዋሪው ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው የሚወያዩባቸው እንጠያየቅ መድረኮች በስፋት መካሔዳቸውንም ኃላፊዋ ጨምረው ገልፀዋል። ወ/ሮ ሲፈን ለተቋሙ ውጤታማነት ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው አካላት በማመስገን በቀጣይም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ያሳሰቡ ሲሆን በግማሽ አመቱ የላቀ አፈፃፀም ለነበራቸው ተቋማትና ግለሰቦች የእውቅና ሽልማት ዋንጫና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል። በዚህ መሠረት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት አፈፃፀም ደረጃ የያዙ ወረዳዎች:- 1ኛ- ወረዳ 8 2ኛ- ወረዳ 4, 7 እና 10 3ኛ- ወረዳ 3, 9 እና 6 በመሆን አጠናቀዋል። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !!

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች