image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት 16,000 ሺህ በላይ ወጣቶች በማሳተፍ በገንዘብ ፦እውቀትና ጉልበት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገለጸ።

ሀምሌ 10, 2018
የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ምክትል ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት በጎ ተግባር በሰውና በፈጣሪ ዘንድም ዋጋ ያለው ነው። በጎ መስራት ለህልውናው የሚሰጠው እርካታ ከፍ ያለ በመሆኑ ወጣቶች ይህንን መልካም ተግባር አጠናክረው መቀጠል አለባቹ ብለዋል። በጎ መስራትን ባህል በማድረግ አቅመ ደካሞችንና አረጋዊያን ለመደገፍ በትብብር መሰራት እንዳለበት የተጠቆመ ሲሆን 18 የትኩረት መስክ የሚሆኑ አጠቃላይ በጎ ተግባራት በልዩ ትኩረት እየተከናወነም እንደሆነ ተናግረዋል። በክ/ከተማው በበጎ ተግባር የሚታወቁ ወጣቶች በክረምት ወራት በጎ ተግባር በንቃት የሚሳተፉበት ወቅት በመሆኑ ልዩ ያደረጋል ብለው የዘንድሮ ክረምት በጎ በንቃት መሳተፍ ያስፈልጋል ብለዋል። በርካታ ወጣቶች የሚሳተፉበት በጎ ተግባር በዋነኝነት የአረንጋዴ አሻራ :ቤት አፍርሶ መገንባት ፥ትራፊክ ፥የክረምት ትምህርት ማስተማር ፥ደም ልገሳ ሲሆኑ አረጋውያንና አቅመ ደካሞችን መርዳትም በመሆኑ ወጣቶች የጀመሩትን በጎ ተግባር እስከሚጠናቀቅ በትኩረት እንዲሰሩ አቶ አሰፋ ቶላ አሳስበዋል። የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ እጅጋየው አድማሱ በበኩላቸው ወጣቶች በክረምቱ በጎ ፍቃድ ያከናወኑት መልካም ተግባር የህሊና እርካታ የሚሰጥ ከመሆኑ ባሻገር ከመንግስት የሚወጣውን ወጪ ማስቀረት እየቻለ ያለ ስራ ነው ብለዋል። ወ/ሮ እጅጋቸውአያይዘውም በጎ ስራ ዓመቱን በሙሉ የምንሰራው ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ገልፀው ወጣቶች በጉልበታቸውና በጊዜያቸው ሰርተው እያበረከቱ ላለው በጎ ስራም ምስጋና አቅርበዋል። በበጎ ፍቃድ የሰው ህይወት ይቀየራል ያሉት ወ/ሮ እጅጋየው ወጣቱ ለማህበረሰቡ የመስራት ልምድን እያጠነከረ ሀገራዊ አንድነትን የመገንባት ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ሲሉ ገልፀዋል። የ2017/18 የክረምት ወራት በጎ ተግባር ከ18ቱ የትኩረት መስኮች እየተከናወነ እንደሆነ ተገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች