image
image
image
image
image

የደብረ ብርሃን ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያው ከልደታ ክፍለ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ።

ሰኔ 14, 2018
የደብረ ብርሃን ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ የከተማዋን ፈጣን የኢንዱስትሪ እና የኢንቨስትመንት ዕድገት ሊመጥን የሚችል ጠንካራና ዘመናዊ የተግባቦት ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ የልምድ ልውውጥ ከአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ጋር አካሂዷል። ​በዕለቱ የልደታ ክፍለ ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሲፈን ባዩ እና የተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተቋማቸውን ግንባር ቀደም እና ተሸላሚ ያደረጉ ዘመናዊ አሠራሮችን ለደብረ ብርሃን ከተማ የኮሙኒኬሽን ልዑካን ቡድን በዝርዝር አቅርበዋል። ​በዋናነት በልምድ ልውውጡ የተቀሰሙ ምርጥ ተሞክሮዎች፦ በ​ዲጂታል ኮሙኒኬሽን የዲጂታል ሚዲያ አማራጮችን ለሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም፤​ የመረጃ አያያዝ ሥርዓትን፤ ዘመናዊና የተቀናጀ የኮሙኒኬሽን መረጃዎችን የማደራጀትና የመተንተን ብቃት፤ ​ሕዝባዊ ተሳትፎና ምላሽ ሰጪነት፤ የኅብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በማዳመጥና በኮሙኒኬሽን አግባብ አፋጣኝ ምላሽ የመስጠት ልምድ እና ​አካታችነት (Inclusivity) ማለትም ልዩ ትኩረት የሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ድምፅ የሚያስተጋቡ የሚዲያ ሥራዎችን ማከናወን የሚሉት ናቸው። ​የተቀሰሙ ምርጥ ተሞክሮዎች ወደ ተግባር እንደሚለወጡ የደብረ ብርሃን ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ይገርማል አበበ በመድረኩ አብራርተዋል። የደብረ ብርሃን ከተማ ግዙፍ የኢንዱስትሪ እምቅ አቅምና መልካም ገጽታ በአግባቡ ለመገንባት ተቋማዊ የኮሙኒኬሽን አቅምን ማሳደግ ወቅታዊና ጊዜው የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። ​ ከአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የተገኘው የተቀናጀ የተግባቦትና የቅንጅታዊ አሠራር ተሞክሮ በቀጣዩ የበጀት ዓመት ዕቅድ ውስጥ ተካቶ ወደ ተግባር እንደሚለወጥም ኃላፊው አረጋግጠዋል። ​የደብረ ብርሃን ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ ያካበቱትን ውጤታማ ተሞክሮ ያለስስት ላካፈሉ እና የላቀ አቀባበል ላደረጉላቸው የልደታ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። መረጃው የደብረብርሃን ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች