image
image
image
image
image

የሚኒ ሚዲያ ክበባት ዋና አላማ ተማሪዎች በስነ-ምግባር የታነፁ ሀገር ወዳድ ዜጋ እንዲሆኑ መስራት መሆኑ ተገለፀ፡፡

ታህሳስ 1, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች እየተሳተፉ ላሉ የሚኒ ሚዲያ ክበብ አባላት እና አማተር ጋዜጠኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሲፈን ባዩ በስልጠና ላይ እንዳሉት ትምህርት ቤቶች የሚኒ ሚዲያ አማራጮችን መዘርጋታቸው ተማሪዎች እውቀት፣ ክህሎትና ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። አያይዘው እንደ ተቋም በሀገር ደረጃ ትልቅ ስራ የሚሰሩ ታዳጊዎችን ለማፍራት ጽ/ቤቱ ሙያዊ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አንስተው የሚኒ ሚዲያ ክበባት ዋና አላማ ተማሪዎች በስነ-ምግባር የታነፁ ሀገር ወዳድ ዜጋ እንዲሆኑ መስራት መሆኑን ገልፀዋል። ተማሪዎች ዝንባሌያቸውን እንዲለዩ በማድረግ ስኬታማ ስራዎችን አብረን እንስራ ያሉት ወ/ሮ ሲፈን ሚኒ ሚዲያዎች ለተለያዩ ሙያዎች ትልቅ ግብዓት ናቸውና ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጧቸው ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡ በጽ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ባለሞያ የሆኑት አቶ አስቻለው ይርሰማ ስልጠናውን ሲሰጡ የሚኒ ሚዲያ ምንነት፣ አደረጃጀት፣ መረጃ አቀራረብ፣ ይዘት ቀረጻ እና ከአጠቃቀም አንጻር ሊያስከትል የሚችለውን አዎንታዊና አሉታዊ ተጽእኖ የተመለከቱ ነጥቦችን አብራርተዋል፡፡ የሚኒ ሚዲያ ክበባት ዋና አላማ በማዝናናት ማስተማር ነው ብለው ተማሪዎች ሀገር ተረካቢ እንደመሆናቸው ሚኒ ሚዲያው፤ ለተማሪዎች በሚመጥናቸው ቋንቋና የአቀራረብ ይዘት ተዘጋጅቶ ሊቀርብላቸው ይገባል ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች